መንገደኛው

ወጌሳ እንዲሆን
ሲቃኘው እውቀቱን
ሲዳስስ መንገዱን
ሲመረምር ፍጥረትን::

ጮሆም ለዓለም
እንዲሰፍን ሰላም
ለምሆን አብነት
ተጋዘም የኛው ወጣት::

ደርሶ-መልስ ቲኬት
አስቆርጦ በስሜት
ጉዞውን ሲጀምር
ድልድዩን ለመሻገር:

በዋሽንት ሲወድስ
በበገና ሲቀድስ
ሃጁ ላይመለስ
ባቡሩ ሲደመሰስ:

ታሪክ ወይስ ተረት
በወጡበት መቅረት
ፋኖ የእሳት ራት
ዕጣህ ሆኖክ ለትእይንት::

ኃ ሥ ዘ

10/24/2006::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *