ኖርን ያላችሁ ሳትወለዱ
ሥር ምሳችሁ ሥር ሳትሰዱ
ያመተ ዓለም ሰዎች ዕድሜ–በላ
                                ተቀጥላ።
በሺ ዘመን እግሮች መውተርተር
በከርሞ ጥጃነት መግተርተር
በልመድ— ልማድ መወጠር
በእምነት —እምነት መጠበብ
በይሉኝታ —ይሉኝታ መታለብ። …