ልጅ ባባቱ ያፌዛል
አባት በልጁ ያለቅሳል
እናት ማሕፀንዋ ትረግማለች
ያጠባችዉን ታጣለች::

የቃኤልን ፅዋ ይቀበላል
ከነምልክቱ ይቅበዘበዛል
ያጠፋውን ይፈልጋል
ማንነቱን ይነፈጋል::

በትዝታ ይኖራል
ታሪክን ይተርካል
ራሱን ያታልላል
በቀልን ይሻል::

መምሰልን ይወዳል
ወጣቱነቱን ይናፍቃል
ሌትተቀን ይፀፀታል
በመድሓኒት ይሸነገላል::

በሁለት ዓለም ተኑሮ
ሀዲሱና የድሮ
በሁሉም ተወጥሮ
ትርፉ ኮነ እሮሮ::

                                              Las Vegas 7 2017

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *