ምንም ነን አንድ ምንም
ሁሉንም ነን አንዱን ብቻ አናምንም
የምንቸረው የልንም እንጂ …
ከማንም ምንም…
ነውር ስለሆነ ብቻ ዘለልነው
ግን … ያለአንቀልባ በልብ አዘልነው

በመጣን … እድሜ ምንም አላሳጣን
በጎን እንደሰው በምድር …
እንደባህር ዓሳ ትን እስኪለን ጠጣን
እቁብ አምጣን … አጥበን አሰጣን
ለሥልጣኔ ሳይሆን ለሥልጣን
አዎ ለሥልጣን …

ከራስ ወዲያ ነፋስ ቢሉን ፋስ አለ
ለኔ ካይኔ በላይ ቢሉን ጀሮ አለ
በእጅ የያዙት ወርቅ አያደምቅ
ቢሉን … ቃል ኪዳን ቀለበት አለ …
ከሞተ አንበሳ የቆመ ውሻ ይሻል
ቢሉን … ይመከር አስከሬኑን ሲያይ ይሻሻል
አፍ ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ
ቢሉን … አለን እኛ ላመነው … አለን እና ሰጥ ለጥ

የት ናችሁ ቢሉን የትም
ጥግ የሌለው ፍጥረት ውስጥ እየኖርን
የማንንም ለማንም አንሰስትም
ከበጀው ያውጅው
ካላውጀው ፈጀው እየሆነብን
ነጋብን ጠባብን ምን አለብን
አላጠባን አላለብን
ለመብረር ምን ክንፍ ይሻል
ዕድሜ ላሳብ ፈረሰኛ

የነቃ ባያመረቃ … የናፈቀም አርፎ አይተኛ
ምን አለህ ቢሉኝ ምንም
ስመጣም ምንጨን አላውቀው
ስሄድም አልተምንም

አጋፔ … ኑሮ
አጋፔ … ዕድሜ
አጋፔ … ፍታት
አጋፔ … ሳታት
እንካን ፈትም ሞኝም አልሳታት

አጋፔ

ሁልም ባለለት ያለምንም
ምንም በሌለበት ሁሉንም
አማካይ ቢሻ
ዋሹ
አካፋይ ቢሉ … ያውለዎት
መስተዎት ፊት ይቁምና
ምስልዎን የሚያሳይ መታዘቢያ አለልዎት

ነጋሪት አያስፈልግም
መቸም እንደልቤ አድራለሁ ብሎ
ምንገድ ያሰማራ ቀለብ
ይንጀት ልሆድ አይነፍግም
ክንፈቁት መቸም አይርቁት
ከጠሉት መቸም እየጠለሉት

እንዲሁም እንዲያም እያለ
ሁሉም ራሱን መሰለ
በስፋቱ ልክ ስፋቱን …
በቸርነቱ ውስጥ ክፋቱን
በልማቱ ውስጥ ጥፋቱን

ሁሉንም ቀን እየገለጠው
ሁሉንም ሌት እየለየው አዋዮው
ሄደንበት ሽቅብ በእንቅብ …
አለት በውንፊት ስናንቀረቅብ
ናኘነው ቁልቁል …
ልንጠነቁል

ሰገርን አግድሙን
ፍቅር ዘውዘው መውደድ ሽሙንሙን
እና … ምን ይሁን
በታየን ፈሰስን … ባልታየን ረጋን
ሁለት ሆንና … ጥንድ እያወጋን
ምንም ብንፈራ … ፍራትን ሰጋን

መጥምቁ ዮሐንስ
ጥር ፺፭

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *