ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ
አይንሽ የጠዋት ጨረር
የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የሥንዴ ራስ ዛላ
አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጀ ነሽ አንቺዬ
እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ
ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለው
እስረኛ ሆኛለው፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *