ሳላስበው ድንገት
ሳልዘጋጅበት

ጨለማን ሰንጥቆ
ብርሃንን ፈንጥቆ

ቀልብን እንደሚስብ
ተውርዋሪ ኮከብ

ቦግ-እልም አልሺና!
ታይተሽ ጠፋሽና!

በብራና ወጥመድ
በፊደሎች ገመድ

ሳልይዝሽ አስሬ
ሳላውቅሽ መርምሬ

የቓመጠው ልቤ
የከጀለው ቀልቤ

ገና አንቺን እንዳለ
እንደተንቀዋለለ

ምነው ደብዛሽ ጠፋ?
አመልሽ ከረፋ?

ወይ ኧንቺ ጉደኛ!
ጭምት፣ ምትሃተኛ
ስቃይ ነሽ፤ ፈተና!

ነሐሴ ፩፱፻፺፰

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *