ልወድስ ወይስ ላልቅስ
ላይ ላዩን ስዳስስ
ውስጡን ሳልቀይስ
ዓይንሽን ሳስታውስ፤
ለካስ…ህልም ኑሯዋል
ራእይ… አይደል…አይደል…
እኔጋ ተቀርጸሽ
ሲንቀሳቀስ… ከንፈርሽ
ታጅቦ በጥርስሽ…
ጤዛ የሆነው ፈገግታሽ።
ምንይሆን..ተስፋ ቢስ…የሆንሺው…
በነሽ…እንደ አቧራ… የቀረሺው
ከገበታው የተለየሺው
ግብአተ መሬት የመረጥሺው፤
ዝናብ አክቦለልሽ
ወይስ ድንግልናሽ…
ሳይነጋ የተጋዝሽ
ብቻሽን የሄድሽ፤
እስቲ ይሁን ልሰናበትሽ
አቅም የለኝ እንዳልመልስሽ
ምንጊዜም…ዓለሜ … እኔውነሽ
ሆኖም…አፈርነሽና…አፈር…አፈርሆንሽ።

                                       1968

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *