የህያዋን ልሣን …
የሰማዕታት ድርሳን…
አኩሱም … የብቃት ስም!
ያረጋውያን ምክር …
የነዳያን ዝክር …
የንፉግ ክርክር …
የጎጆ ፉክክር …
ማተብ ባንገት ሲውል ታሠረ ባንድ ክር!
በሦስትዮሽ ህብር …
በደሙ እንዲከብር …
ባመነበት ሊያብር …
ለሕይወት ሊገብር …
ህብር …
የህያዋን ልሳን
የሰማዕታት ድርሣን …
አኩሱም … የብቃት ስም …
ዕምነትና ዕውነት …
ሰውና ሰውነት …
አኩሱም … የብቃት ስም …
አንዱ ላንዱ ቆሞ …
አንዱ ላንዱ ሞቶ …
ፍቅር ተሸምቶ … ብይን ተገምቶ …
አልሰሜንም አምቶ …
ብሎም ለራስ ጉዳይ … ብሎም ላንጀት ግዳይ …
ባይዘሩትም ይበቅላል እንደበልግ እንጉዳይ …
አኩሱም የጧት ፀሓይ …
የብርሃን ለሐይ …
የግንባር ምስክር …
የዕምነት የፅናት ክር …
የህያዋን ልሣን
የስማዕታት ድርሣን
አኩሱም … የንጋት ስም …
ባይን አይቶ ለይቶ …
እህ ብሎ ሰምቶ …
እንደሰም ተስማምቶ …
ስውር የከሰት … ህቡዕ የገለጠ
ካስብ ፍጥነት በላይ … ቀድሞ ያሰለጠ …
በነፍስ የታደመ … ከንውር ያመለጠ …
ዕምነትና ዕውነት
ሰውና ሰውነት …
አኩሱም … የፅናት ስም …
‘ርጉምን ታግሶ …
ንፉግን ደግሶ …
አፈናን አንግሶ …
በሦስትዮሽ ህብር …
በደሙ ሊከብር
ባመነበት ሊያብር
ለሕይወት ሊገብር …
አኩሱም … የህብር ስም …
ስርየትን ከፅርፃት …
ፍቅርን ከይቅርታ …
ንቃትን ከእምርታ …
በህያዋን ህዋ … በሰማዕታት ተርታ …
እኩል ተሰልፎ …
ፈተናውን አልፎ …
እንደሰንደቅ ቆመ
ብቃቱን ጠቆመ!
ዝማሬውን ካዕዋፍ …
ቅኔውን ከቀን ጧፍ…
ማህሌቱን ከአፀድ …
ገድ አለን ግዴታ …
የህያው ውዴታ …
ከተፈጥሮ ታርቆ …
አሻግሮ ሲያማትር … ሲመረምር ጠልቆ …
ሲያስተውል አርቆ
ትንቢቱ ንግሩ …
የዕድሜ ሽግግሩ …
በጊዜው ለሚዜው …
አንደበቱን ከፍቶ … ቃል አመሳጠረ …
ሰማዕት በቀለ … አኩሱም ሰው ፈጠረ …
እንደወርቅ በሳት … በጋመው ነጠረ …
ደሞ አነጣጠረ …
አለ አኩሱም …
በኛው ከኛው ለኛው …
በኛው ስም … በኛው ስም …
ምድር ጦም አይደር …
አገር አይበደር …
ወራቱ መብራቱ …
እራቱ ኩራቱ …
ሠላሙ ፍራቱ …
በሸክላው ባራቱ …
ይጠገንለታል እንደስብራቱ …
ለነገ ብሥራቱ …
አለ አክሱም
በምፅዓት ስም …

ምዕራፍ ሁለት!

እንግዲህ … ከእጅህ በጉንጭህ …
ኃላ እንዳይቆጭህ …
ምግባር እስኪያጭህ …
እንኳንስ ራብ አሞራ ይንጭህ!

ታህሳስ 96 …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *