በነዘህላል ለነሩኩባት
ዘመን ለቆጠርኩባት
ትላንት…ትላንት…
ዳግም ባገኘኃት
ሳይመሽብኝ በጠየቁዃት
የምሬን ባጫውትካት።

አሉሄ… አሉሄ…ልበል ለማኑን….

ለክርስቲያን ካህኑን
ለራባይ አይሁድን
ለሼኩ ሙስሊሙን
መንገደኛዉ ደብተራን
ሊሰሙኝ ኑዛዜን?

እነሱም…ነደሩ…ተናገሩ…

ንስሃ ገብተህ
ሂስን ተቀብለህ
ድካማነትህን ገልፀህ
በውሃ ታጥበህ
በወይን ትነፃለህ።

ቢሉም…ቢሉም…ወኪል ቢሆኑም

ላልደግም ዳዊትን
ላላነብ ቁርዓንን
ላይገባኝ ማህሌትን
ሚስጡሩን ዖሪትን
እንዲሁም ሓዲስን
ምን ይሁን… ምን…
እንዲያው..እንዲያው….ይሁን…
ልበል… ለይኩን…ለይኩን……

2013

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *