የቱ ይሆን ኩኒኔው፣ የትኛው ነው ፅድቁ?
የምድሩ የቅርቡ፣ የሰማዩ የርቁ?
በእንጀራ በጠላ በሥጋ ሢሣይ፣
አካል ብቻ እንጂ፣ ነብስ አታድግም ወይ?
ነብስ አንደነበልባል፣ ሥጋ እንደእንጨት፣
አይደል ብንድ ዕጣቸው፣ መዳፈን መብራት?
መክሰል ወይ መፈካት?
የት ነው የሥጋ ደብሩ፣ ደሞ የነብስ ቤት?
መቸ ነው ለየብቻ የትካለሉት፣ ጎጆስ የወጡት?

ልሂድ – ልሂድ አለች፣ ወደ ሕልሟ ኬላ፣
ሥጋ ሐር ልብሷን ነብሴ አውልቃ ጥላ፣
ከፅድቁ ገበታ፣ ከአብርሃም ልትበላ።
ተይ አይሆንም ነብሴ፣ ሥጋሽ ይታሠብሽ፣
ተመከሪ ነብሴ፣ ጭቃው ነው ገነትሽ፣
የዘላለም ቤትሽ።

1966

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *