ሕልም አይሉት ቅዠት፣
ሕልም አይሉት ቅዠት—-ኑሮ አይባል ሞት
በህላዊ ለኮ በልማድ ሰንሰልት
ስሳብ ስጎተት፤
የሸረሪት ድሬ እያፈተለከ
ዘሀው ተበጥሶ
ስቀጥል ዐይነስቤ ፈሶ፤
እንደው በደለማ ስቀመጥ ስነሳ
ራዕይ ቀረብኝ ልቤን የሚያሳሳ።-
“በለስ ለመለመች፣በ.ለ.በ.ለ.”
                   እያለ አወጋኝ
በቀኑ ደለማ ሌሊቱ ተጣባኝ።

በደካማ ጎኔ በድሁር መንፈሴ
ባካተተ ወኔ በባከነ ቅርሴ
ምኑን ከምን ይዤ፣እንደምን አድርጌ
በለስን ልጠብቅ፣ ራሴን ታድጌ?

መለከት እምቢልታው ጩኸቱ ሰቀቀኝ
በነገ ዲብ ጮኸ ዛሬ አደነቆረኝ
ከዘመኑ ቀድሞ ዘመኔን ደሰመኝ።

ጊዜ ይሮጥ ጀመር ዛሬስ ወደኃላ
ከርሞ ይጋጭ ጀመር ከዛሬ ከሰላ
ውሉዳነ ዘመን –
ይዋጉ ጀመረ ዛሬና ነጋቸው
በሰዎች ራስ ቅል፣ ደግሞም ባጥንታቸው።
ዛሬ አመድ መስሎ ነጥቶና ገርጥቶ
ከዐዋዩ ተፋቶ፣
የነገን ጨካኝ ክንድ፣ እሣት የለበሰ
ሲተባ ሲፈራ እየተላኮሰ፣
ሲዋጉ – ሲፋጩ ተግተው ሰዳሰሙ
እኔን ነው እሚመስል፣ ደማቸው ቀለሙ፤…

ለዚህ ነው እሚያመኝ፣ዘልቆም እሚወጋኝ
የነሱ መሸበር እንቅልፌን የነሣኝ
“በለስ ለመለመች” ራዕይ የገፋኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *