ሲጠራ አቤት ብሎ የተማረ
ሲልኩት ወዴት ብሎ የዘመረ
ሲያዙት አንዴት ብሎ የመረመረ
ሲመረጥ ተመርቆ
ከልቡ አይርቅም ርቆ
ውሉን አይስትም ረቆ
ማመን ከመስማት ነውና መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል
ተጠርቶ የተማረ ተመርጦ የተመረቀ
እንደፋኖ ድርብ ድግ ቅኝት
ያንጀቱን ባንጀት ያጣብቃል
የልቡን ባይኑ ይጠብቃል
ሲማር …

በህግ ልቦና ጥበብ እድሜን እንደሺማኔ ደውሮ
እንካን ወደሚሄዱበት በአይነ ህሊና
ቅድመ ዓለም ተወርዉሮ
ከራሱና ከምኞቱ ተሰውሮ
አባትና እናት እንዳቀደ
በራሱ ከቀለድ
ባሰቡት ልክም ባይሆን … የእውነት አነጣጥሮ ለመጣል
ሰው ሆኖ ከተፈጠረ … ለጥሬ ዱለት ባይበቃም
ወንድ ልጅ አሞት መች ያጣል
ራስ የሚችል እንገት
ሽቅብ የሚቃትት ጉልበት
ቢላ እማይደፍረው ጉበት
እሱማ አለ እንጂ አለበት!

ለወለደችው የታዘዘ … ለፈጠረው ያጎነበሰ
ለለቱ ፈረስም ብንል … አድሮ ይጠድቃል እንጂ
አፈር በልቶ መች በሰበሰ
አታዩትም ደምሰውን ወንድሙን እንካ ደስ ያለህ ለማለት
ባለበት … በዋለበት
በሌለበት … ፅንፈአለም እስኪሰማለት
በፍቅር ልቡ ደማለት
እና … ይችን ቀን የባረከ
ቤዛ አለም አማኑኤል … ፍቅሩን ባቡ ላይ ተረክ
ወልዶ መሳምንና … ዘርቶ መቃምን ለሰጠው ሰው
ምን ቀረኝ ብሎ ያዝናል … ሰማይና ምድር ከተዋሰው
ለፅድቁ አንድምታ ምልት
ክንዱን አዝሎት እንዳይመክት
ከልጆቹ አንዱን በሞት ተነጥቆ
አንዱን ያስመርቃል ለጥቆ
የልጅም አሥራት አለውና … መለኮት መርጦ ለወሰደው
ሳይጠግን አይሰብር ጌታ …

ከጠራአቸው መኃል ለይቶ ለምረቃ ፈቀደው
የወለደ አንጀት ባይችልም .. ኃዘን መብቃቱ ግን ግድ ነው
እና ሁሉም ይበቃል … የሄደም አለበት ይቅናው
ያለም በፍቅር ይጠብቃ

አቡ እናትህ እንዳታዝን … ካይንና ከልባ አትራቅ
አባትህ እንዳይነቅፍህ …ላመንክበት ቀጥበል
ተግ በል እንደ ብራቅ
ወንድምህ እንዳይንቅህ
ልብህ ብቻ ይሁን ሥንቅህ
በድል ብቻ ይሁን ትጥቅህ
እህተ እንዳታፍርብህ
ክንድህን ሳትንተራስ
የነፍስህ እጦት እንዳይርብህ
ወዳጅህ እንዲኮራብህ
ከቃልህ አትጉደል … ሳታት ቁም በምኩራብህ
ጠላትህን አንተው ፈልገው
ለሱም ቢሆን እንተነትህን ምን ብትሰስት አትንፈገው
ሰሜት እንደ ድንጉላ ፈረስ … ሽምጥ ማስጋለቡ ባይቀር
ወንጀል አይደለም ማፍቀር
ሁሉም በእርሱ ነውና … እሱ ያልገባበት ስለማይሰምር
በጥርጣሬ እየፍረጅክ … ኃሳብህን ባሳብ አታስምር

አሁን ደሞ አንተ አለኩት ቅድም አንቺ ብዬ
የኔን ለሱ ትቼ የሱን ተቀብዬ
ልምጣ ወይስ ልቆይ … የቱ ይሻለኛል
ከነበረ ይልቅ … ዓመተ ይለያል
ሙሌ አንዴ ይለኛል … አብርሃም ወንድሜ
ቆሞ የሚተብቀኝ … እኔ ተጋድሜ
ሰፋ አርገው ቦታውን … መቼም መምጣቴ አይቀር
ከሞት አያስጥልም … ወትሮም ናሪ ማፍቀር
መስፍኔ ሽቅርቅር
እንደ ቡን እንደ ጫት ስትይኝ ቅርቅር
የጠናብኝ ለታ
አለሁ አለሽበት … ለፍቅርሽ ውለታ።

ተረት ሰፈር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *